የተቋሙ ስልጣን ፤ ተግባርና ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
የኢንተርኘራይዞች የሥራ ፈላጊዎችንና የስራ ገበያ መረጃ ይመዘግባል፤ መረጃ ይሰበስባል፣ ይተነትናል፣ ያደራጃል፣ ይተነትናል ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፤
የኢንተርኘራይዞች የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ያቋቁማል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤
ኢንተርኘራይዞች በንግድ ህጉ እና አግባብ ባለው ሌላ ህግ መሰረት ያደራጃል፤ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤
በኢንተርኘራይዝ ለተሰማሩ አንቀሳቃሾችና አምራቾች የሙያ ማበልፀጊያ ስልጠናዎች እና አውደ ርዕዮች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤
ኢንተርኘራይዞች ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከጥናትና ምርምር ተቋማት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ይሰራል፣
ኢንተርኘራይዞች የመረጃ፣ የቴክኖሎጂ መረጣ፣ የድርድር፣ የግንባታ፣ የኮሚሺኒንግ ድጋፍ ይሰጣል፤ ውጤቱንም ይገመግማል፤
ለኢንተርኘራይዞች የመረጃና የምክር አገልግሎት የሚሰጥበት የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፤
የኢንተርኘራይዞች የብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም የደረጃ እና የጥራት ሰርቲፊኬሽን እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጋል፤
ኢንተርኘራይዞችን ከጥቃቅን ወደ አነስተኛ፤ ከአነስተኛ ወደ መካከለኛና ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ እንዲሸጋገሩ ያደርጋል፤
ኢንተርኘራይዞች ተወዳዳሪ ለማድረግ በጥናት ላይ የተመሰረተ የማበረታቻ፣ የዕውቅና እና ሽልማት ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
የኢንተርኘራይዞች በዘርፍ ማህበራት ያደራጃል፤ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፤
ሥራና ሠራተኛ ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ በህግ መሰረት ይሰጣል፤ ድጋፍ ያደርጋል፤ መሥራታቸውን ያረጋግጣል፤ ይሰርዛል፤
ሥራና ሠራተኛ ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች እና የግል የስራ ሁኔታ ቁጥጥር አገልግሎት አቅራቢዎች የብቃት ማረጋገጫ መስጠት፤
ስለውጭ አገር ሥራ ስምሪት እና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራዎችን መስራት፤
ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
- የሥራ ስምሪት በማስፋፋት የስራ ዕድል መፍጠር
- ለኢንዱስትሪ ልማት መሰረት የሚጥል ዘርፍ እንዲሆን ማስቻል፣
- በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚ ማድረግ
- የመስሪያ ቦታ ልማትና አቅርቦት
- ምቹ የሥራ ቦታና አካባቢ መፍጠር